top of page
Search
  • mastu89

የእውቀት ሽግግር በቴአትር ጥበባት ትምህርት ቤቶቻችን

ከዚህ ቀደም በታተመው ፅሁፍ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ስለተደረገው መጠነኛ የእውቀት ሽግግር በአጭሩ አስነብበን (https://www.southomotheatre.com/post/%E1%8B%A8%E1%8A%A5%E1%8B%8D%E1%89%80%E1%89%B5-%E1%88%BD%E1%8C%8D%E1%8C%8D%E1%88%AD-%E1%89%A0%E1%89%B4%E1%8A%A0%E1%89%B5%E1%88%AD-%E1%89%A4%E1%89%B6%E1%89%BB%E1%89%BD%E1%8A%95) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ሁኔታ እንደምናስቃኛችሁ ቃል ገብተን ነበር በዚህም መሰረት ኩባንያችን በአዲስ አበባ እና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች የነበረውን አጫጭር ቆይታዎች እናጫውታችሁ።

የሀገራችን የቴአትር እድገት አንድም በባለ ተሰጦዎች ሁለትም በሳይንሳዊ መንገድ ተንትነው በቴክኒክ አዳብረው በሚያቀርቡ ምሁራን እጅ ስር መሆኑ አጠያያቂ አይደለም። ጥበቡን በሳይንሳዊ ሂደት የሚበልቱት ምሁራኖቻችን ታዲያ የአለማችንን የቴክኖሎጂና እና የፈጠራ ምህዋር ተከለው በፍጥነቱ ልክ መጓዝ ካልቻሉ አሊያም የኔ የሚሉትን አዲስ ነገር ፈጥረው ቀድመው ካልተገኙ ጥበቡ ገደብ የለሽ ነውና አብሮ መጓዝ ሊያዳግት፤ አንዳንዴም ነገራችን ‘ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲል’ ሊሆን ይችላል እና መንቃት ያስፈልጋል። ደቡብ ኢትዮጵያ የቴአትር ኩባንያም በዘመኑ ያለውን የመብራት ግብአት ስርጭት ቴክኖሎጂ ለሀገራችን ምሁራን ለማስተዋወቅ፣ ካወቁት ጋር ደግሞ በጋራ ለመምከር በማሰብ በሁለት ዩኒቨርሲቲዎች የሁለት፣ ሁለት ቀን ‘ወርክሾፕ’ አዘጋጅቶ ነበር።


ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የነበረው ወርክሾፕ በተማሪዎቹ እና መምህራኑ ተሳትፎ የደመቀና በርካታ የውይይት ሀሳቦች የተነሱበት ከመሆኑም ባሻገር 735 ኪሜ አቋርጠው በመጡ የዘመኑን እውቀት በተጠሙ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት መምህራን ተሳትፎም ያሸበረቀ ነበር። የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችም እንደ ሰነፍ ተማሪ መደበቂያ የሚቆጠረውን የመብራት ስርጭት ስራ ምን እንደሆነ በተጨባጭ ተረድተው ቀጣይ የጥበብ ጉዞዋቸውን በመብራት ስርጭት ዲዛይነርነርት ለማስቀጠል ማቀዳቸውን መስማት የዚህችን አጭር ‘ወርክሾፕ’ ጠቀሜታና ስኬት ያረጋገጠ ነበር።

የተሳካ ‘ወርክሾፕ’ እንድናደርግ ለተባበሩን የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊልን፣ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል ሀላፊ አቶ ሽኩር ናስርን እና መላው የትምህርት ክፍሉን መምህራን እና ተማሪዎች እንዲሁም ከረጅም ርቀት የመጡትን የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ መምህራንን እጅግ ማመስገን እንወዳለን።


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የነበረው ‘ወርክሾፕ’ ለሁለት ቀን ታቅዶ ለአንድ ቀን ብቻ የተካሄደ ቢሆንም ይህ እንዲሆን እጅግ ለደከሙት የዩኒቨርሲቲው መምህራን ወ/ሮ እየሩሳሌም ካሳሁን፣ አቶ አንተነህ ሰይፉ እና አቶ ቢኒያም ከተማ እንዲሁም ለቴአትር ትምህርት ክፍሉ ተወዳጅ ፀሀፊ የኔነሽ (የንዬ)፣ ‘ወርክሾፑን’ ለተሳተፉት የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችም እጅግ የላቀ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

በቀጣይ ደግሞ በሌሎች ዘርፎች እንደምንገናኝ እምነታችን የላቀ ነው። ቸር ይግጠመን







23 views0 comments

Comments


bottom of page