top of page
Search

የወዳጅነት ብሩህ ጉዞ!

mastu89

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና በደቡብ ኦሞ ቴአትር ኩባንያ መካከል በጋራ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ፊርማ ተፈረመ። የፊርማ ስነስርአቱ የተካሄደው ሚያዚያ 11/2014 ዓ.ም ነበር።


ስምምነቱ ሁለቱን አካላት በቴአትር ጥበባት፣ በልቦለዳዊ እና ዘጋቢ ፊልሞች ላይ እንዲሁም በጥናት እና ምርምር ላይ በጋራ ለመስራት እንደሚያስችላቸው ተገልፁአል።


ዩኒቨርሲቲው እና የቴአትር ኩባንያው አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ያላቸው ሀገር በቀል የቴአትር አቅርቦቶችን፣ ችግር ፈቺ የጥናት እና ምርምር ውጤቶችን፣ እንዲሁም ዘጋቢ እና ልቦለዳዊ ፊልሞችን አዘጋጅተው ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ መድረኮች ማስጥራት እንዲችሉ እድል ይፈጥራልም ተብሏል። ስምምነቱ የሁለቱንም አካላት እኩል ተጠቃሚነት ከማረጋገጡም በላይ የቴአትር ኩባንያው በዩናይትድ ኪንግደም ከሚገኙ ሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በመጣመር ለዩኒቨርሲቲው ርዕይ ስኬት የበኩሉን እንዲወጣ ያስችላል።


ስምምነቱን የፈረሙት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፋሪስ ደሊል (ዶ/ር) እና የደቡብ ኦሞ ቴአትር ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ቤን ያንግ ናቸው።


ይህ ስምምነት እአአ በ2019 በሁለቱ አካላት መካከል ተፈርሞ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።








14 views0 comments

Recent Posts

See All

Comments


bottom of page