top of page
Search
  • mastu89

‘መሬታችን’ አሸነፈ!

Updated: May 14, 2022

የደቡብ ኦሞ ቴአትር ኩባንያ (ደኡቴኮ) መስራች አባል ጋዜጠኛ እና የፊልም ባለሞያ አሌክሳንድራ ጀኖቫ (https://twitter.com/Alexandraaa_cg) ፅፋ እና አዘጋጅታ ያቀረበችው ‘መሬታችን' የተሰኘው አጭር ዘጋቢ ፊልም በ2022ቱ የብሪቲሽ አካዳሚ ኦቭ ፊልም ኤንድ ቴሌቪዥን አርትስ (ባፍታ) በአጭር ፊልም ምድብ አሸናፊ ሆኗል።


ፊልሙ በእንግሊዝ ሀገር የሚኖሩ ጥቁር አርሶ አደሮችን ታሪክ፣ ውጣ ውረድ፣ እና በነጮች የበላይነት ከሚመራው የግብርና ስርአት ጋር የሚያደርጉትን ትንቅንቅ ያስቃኘ ነበር።


አሌክሳንድራ ባለፉት ጥቂት አመታት እንደ ህትመት ጋዜጠኝነቷ እና ፊልም ባለሞያነቷ በዩናይትድ ኪንግደም ያሉ የምግብ እና ግብርና ታሪኮችን የትኩረት ማዕከሏ አድርጋ በመስራቷ በሀገሪቱ የግብርና ዘርፍ ውስጥ ያለውን የነጭ የበላይነት በጥልቀት የመረዳት እድል ገጥሟታል። በዚህም የጥቁሮችን መቋጫ የሌለው የሚመስል መከራ ለአለም ለማሳየት ቆርጣ መነሳቷን ታስረዳለች።


ደኡቴኮ በፊልም ጥበብ እጅግ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበች ላለችው አሌክሳንድራ እንኳን ደስ አለሽ ለማለት ይወዳል!

የብሪቲሽ አካዳሚ ኦቭ ፊልም ኤንድ ቴሌቪዥን አርትስ (ባፍታ) 2022 አሸናፊ የሆነውን ፊልም ለመመልከት የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡



10 views0 comments
bottom of page